በፊንፊኔ አዳራሽ ሆቴል ተብሎ የሚጠራው አስደናቂው ጥንታዊ ህንጻ ከእንጨት የተሰራ ባለ ደረጃ መወጣጫ ያለው ምድር እና ፎቅን የያዘ እና የተለያዩ ባህላዊ እሴቶችን የሚያሳይ ቦታዎችን የያዘ ውብ ሬስቶራንት ሲሆን በውስጡም ጣፋጭ እና ተወዳጅ ባህላዊ ምግቦች እና መጠጦች የሚቀርቡበት እጅግ ማራኪ ስፍራ ነው፡፡
በፊንፊኔ አዳራሽ ሆቴል ውስጥ ለዓይን የሚማርኩ ምስሎችን የያዘ ሲሆን ግቢው አይነግብ የሆኑ አረንጓዴ ቦታዎች ያካተተ ልዩ መስዕብ ያለው በመሆኑ የመንፈስ እርካተ ይሰጣል፡፡
በባህላዊ አዳራሽ ሆቴሉም ዘወትር እሮብ እና አርብ እንዲሁም በፆም ጊዜያት ተወዳጅ የፆም ቡፌ ያዘጋጃል፡፡
በፊንፊኔም ሆነ በአዲሱ ፍልውሃ ባሉት ካፍቴሪያዎች ፈጣን ምግቦች ፣ ትኩስ እና ለስላሳ መጠጦች ለደንበኞች ያዘጋጃል፡፡
በፊንፊኔም ሆነ በአዲሱ ፍልውሃ ባሉት ካፍቴሪያዎች ፈጣን ምግቦች ፣ ትኩስ እና ለስላሳ መጠጦች ለደንበኞች ያቀርባል፡፡
በፊንፊኔ አዳራሽ ሆቴል 25 የመኝታ ክፍሎች ያሉት ሲሆን ከተሟላ መስተንግዶ ጋር አገልግሎት ይሰጣል፡፡
ስብሰባዎች እና ዝግጅቶች
ሆቴላችን እስከ 500 እንግዶችን ለማስተናገድ የሚችል ሁለት የመሰብሰቢያ ቦታዎች አዳራሽ/ ያሉት ሲሆን አዳራሹ ለተለያዩ ግብዣዎች፣ ስብሰባዎች፣ ሠርግ፣ ቀለበት መጠቀም የሚያስችል ቦታ ሲኖረው በተጨማሪም ከግቢ ውጭ ባሉበት ቦታ ከተሟላ መስተንግዶ ጋር አገልግሎት /Catering Service/ይሰጣል፡፡