የጨረታ ማስታወቂያ

ጨረታ ማስታወቂያ
ለመጀመሪያ ጊዜ ጨረታ የሚወጣ የእቃ/የአገልግሎት ግዥ
የፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት ከዚህ በታች የተገለጹትን የእቃ/አገልግሎት ግዥ ለመፈጸም ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። በዚህ መሠረት፦
ሎት 1፦ የፕሪንተር ፎቶ ኮፒ ማሽን ስካነር ጥገና እና ቀለም ሙሉ ግዥ
ለሁለተኛ ጊዜ ጨረታ የሚወጣ የእቃ/አገልግሎት ግዥ
ሎት 2፦ የፓወር ኢንቨርተር (Power Inverter) ጥገና አገልግሎት
ተጫራቾች የሚከተሉትን መመሪያዎች ማሟላትና ተግባራዊ ማድረግ አለባቸው፦
ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበት ሕጋዊና የታደሰ የ2018 ዓ.ም የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ስለመክፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ TIN እና VAT ሰርተፊኬት ያላቸው፤ የገቢዎች ከቢሮክራሲና ጨረታ ለመሳተፍ ከሀገር ውስጥ ገቢ የተሰጣቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር በአቅራቢዎች ዝርዝር ምዝገባ ፈቃድ የተመዘገቡበት የቅርብ ጊዜ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
ተጫራቾች በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ የሥራና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት የታደሰ ፈቃድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት ፌዴራል ፖሊስ የግል የጥበቃ ተቋማት ብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት የታደሰ ፈቃድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 25,000.00 (ሃያ አምስት ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ብቻ ማያያዝ አለባቸው።
እያንዳንዱ ጨረታ ሰነድ መግዣ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በድርጅታችን አዲሱ ፍልውሃ ሆቴል እንግዳ መቀበያ በመክፈል ከድርጅቱ ግዥ አቅርቦት ቡድን መሪ ቢሮ ቀርበው የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
ተጫራቾች የሚሰጡት ዋጋ ከቫት በፊት ወይም ከቫት ጋር ተብሎ በኢትዮጵያ ብር መገለጽ አለበት። ተጫራቾች በጨረታ ሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውን፣ ሙሉ አድራሻቸውን፣ ፊርማቸውንና ማህተም ማሟላትና ማቅረብ አለባቸው።
ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታ ሰነድ ላይ የተሰጠ ዋጋ መቀየር አይቻልም። ዕቃው የሚቀርብበት ጊዜ፣ በታሪፍ ዋጋው ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ መግለጽ አለበት። ስለ ዕቃው ዋስትናና የዋስትና ጊዜ በግልጽ መግለጽ አለበት።
ጨረታን በሚመለከት ለማሸነፍ እንዲረዳዎት ለማንኛውም ኃላፊና ሠራተኛ መደለያ የሰጠ ተጫራች ከጨረታ የሚሰረዝ ሲሆን አሸናፊም ውሉ በቁም ወይም ሙሉ በሙሉ ይሰረዛል።
ድርጅታችን የዋጋ ለውጥ ሳይኖር በመጠን ወይም በዋጋ እስከ 25% በመጨመር ወይም 20% በመቀነስ መግዛት እንደሚችል በቅድሚያ ሊታወቅ ይገባል።
ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ ከቫት በፊት ወይም ከቫት ጋር በግልጽ በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ድረስ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ። ጨረታው በዕለቱ 4:30 ይከፈታል።
ተጫራቾች በሚወዳደሩበት የግዥ ዓይነት መሠረት የተሟላ የቴክኒካልና የፋይናንሻል በተናጠል የጨረታ ሰነድ (Bid document) መሠረት ጨረታ ሰነዶቻቸውን ማዘጋጀት ይኖርባቸዋል። የጨረታው ቴክኒካል ፕሮፖዛል ሰነድ ለብቻው፣ የጨረታ ማስከበሪያ (CPO) ለብቻው እና የፋይናንሻል ሰነድ ለብቻው በጨረታ ሣጥኑ ማስገባት አለባቸው።
የጨረታ ሂደት የቴክኒክ ግምገማ ሌሎች፣ ድርጅቱ በሚያወጣው መስፈርት መሠረት የቴክኒካል ዶክመንት ግምገማና የድርጅታዊ ብቃት ግምገማ ውጤት (60%) እና የፋይናንሻል (ዋጋ) ግምገማ ውጤት (40%) ሲሆን፤ እንደዚሁም ለሌሎች ድርጅቱ Specification ግምገማ (40%) እና የፋይናንሻል (ዋጋ) ግምገማ ውጤት (60%) ድምር በሚያወጣው ስፔሲፊኬሽን መሠረት አሸናፊ የሚለይ መሆኑን ማወቅ አለባችሁ። ነገር ግን ቴክኒካልና ስፔሲፊኬሽን (Specification) ግምገማ ሰነድ ወይም ድርጅታዊ ብቃት ግምገማ ያላለፉ ተጫራቾች የፋይናንሻል ዶክመንት እንደማይከፈት ይታወቃል። የመገምገሚያ መስፈርቱ በዝርዝር በጨረታ ሰነዱ ማየት ይቻላል።
ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ፦ በስልክ ቁጥር 0115 53 07 67 / 0115 15 73 37 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

Spa Service Enterprise

ፍልውሃ አገልግሎት

በብሔራዊ ቤተ-መንግሥት አቅራቢያ, አዲስ አበባ

የስራ ሰዓት፦ከሰኞ እስከ እሁድ -ከጠዋቱ 12:00 ሰዓት እስከ ማታ4:00 ሰዓት

ጠቃሚ ሊንኮች