ድርጅታችን በአካባቢያችን ለሚከበረው የኢሬቻ በዓል ለሚያልፉ እንግዶች የሚሆን ውሃ፣ ዳቦ እና ቆሎ በማዘጋጀት ለሊቱን ሙሉ ለሚያድሩ ደንበኞች እና እንግዶች ተገቢውን አገልግሎት ሰጥቷል። እንዲሁም ድርጅቱ ለሚሰጠው አገልግሎት ተጨማሪ ድጋፍ ይሆን ዘንድ ሆቴሉን እና መታጠቢያ ቤቶችን ክፍት በማድረግ እንግዶች በአግባቡ እንዲጠቀሙበት አድርጓል። በቦታው ላይ በመገኘት ለሊቱን ሙሉ ለሚያድሩ እንግዶች አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረግ የበዓሉ ትክክለኛ አጋር መሆኑን አሳይቷል። በዓሉ በአካባቢያችን በድምቀት የሚከበር በመሆኑ፣ ለበዓሉ ልዩ ድምቀት የሚሰጡ ባንዲራዎችን በመስቀል አካባቢውን አሸብርቋል። እንግዶች የድርጅታችን የቅርብ አካል መሆናቸውን በመገንዘብ እና ከተለያዩ አቅጣጫ ለሚመጡ ወገኖች ማህበራዊ ኃላፊነታችንን ለመወጣት ይህንን ተግባር ማከናወን አስችሎናል። በዓሉ በሚከበርበት ወቅት በርካታ እንግዶች ወደ አካባቢው እንደሚመጡ በመገመት ሰፊውን ቁጥር ያለው እንግዳ በተሳካ ሁኔታ ለማስተናገድ በቂ የሰው ሃይል ተመድቧል። መንገዶች በሚዘጉበት ጊዜ እንግዶችና የሚታጠቡ ሰዎች እንዳይቸገሩ ለሰራተኞች ክፍሎች ተዘጋጅተው በጠዋትም ሆነ በማታ በሚመጡ ሰራተኞች አማካኝነት አገልግሎቱ ለሊቱን ሙሉ እንዲሰጥ ተደርጓል። በተጨማሪም በቦታው ላይ ትኩረት ተሰጥቶ ሰንደቆችና የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክቶች ተሰቅለው እንግዶችን በደማቅ ሁኔታ በመጠበቅ ላይ እንገኛለን፤ አሁንም ሰራተኞቻችን በቦታው በመገኘት አገልግሎቱን በመስጠት ላይ ይገኛሉ።

To honor the vibrant celebrations in our vicinity, we decorated the surrounding area with festive flags and welcoming banners. Driven by a deep sense of corporate social responsibility and a commitment to our community, we were proud to serve the many visitors arriving from various directions.

Anticipating large crowds, we deployed adequate staff to handle the high volume of guests seamlessly. To overcome road closures and ensure uninterrupted service, employee lodging was arranged on-site, enabling day and night shifts to maintain 24/7 operations. In addition to displaying decorative flags and welcoming messages, our staff remains actively on the ground, delivering continuous and dedicated service to all our guests.

Previous የፍልውሃ ስፓ አገልግሎት ድርጅት ማኔጅመንት እና ሰራተኞች በሩጫ ተሳትፎአቸው ጤናን እና አንድነትን አጎለበቱ

የፍልውሃ ስፓ አገልግሎት ድርጅት

ፍልውሃ አገልግሎት

በብሔራዊ ቤተ-መንግሥት አቅራቢያ, አዲስ አበባ

የስራ ሰዓት፦ከሰኞ እስከ እሁድ -ከጠዋቱ 12:00 ሰዓት እስከ ማታ4:00 ሰዓት

ጠቃሚ ሊንኮች